Menelik the II

Menelik II founded the first 

 1. 1894 Addis Ababa –Djibouti railway
 2. Electricity to Addis Ababa,
 3. The first Pharmacy in Addis Ababa on Dec 1st, 1910.
 4. Modern bank in Ethiopia, the Bank of Abyssinia
 5. Modern postal system
 6. Motor car
 7. Modern plumbing.
 8. Telephone
 9. Telegraph
 10. The 1890s, modern method of executing criminals using electric chairs (3)

__________________________________________________________________________________________

 1. መጀመሪያጊዜ መኪና ወደ ኢትዮጵያ ያስገቡ ምንሊክ ናቸው::

ማተምያ መኪና በ 1889 ዓም ፈረንሳይ ነጋዴ የመፃሐፍት ማተሚያ መኪና አምጥቶ ነበር። ይህም ባንዳንደ ተቃውሞ ምክንያት ከሥራ ላይ  ሊውል አልቻለም። በዚያ ዘመን አበዛኛው የኢትዮጵያ መኳንንትና ቀሳወስት ዘመናዊ ጥበብ ሁሉ የሴጣን ሥራ  እየመሰላቸው ይቃውሙ ነበር ስለዚህ ፈረንሣዊው ያመጣው የማተሚያው መኪናም ሥራ ሳይውል ቀረ::
ይህን የተገነዘቡት ዳግማዊ ምንሊክ ቀስበቀስ የዘመናዊ ጥበብ ተቃዋሚዎችን በምክርም በጨዋታም ካሰለጠኑ ብኋላ የሲሪያው ነጋዴ ኤዴልቢ የማተሚያ መኪና እንዲያስመጣላቸው አዘዙት። ኤድልቢም በታዘዘው መሠረት የማተሚያው መኪና ዓ ም መጥቶ ሥራውን ጀመረ።
ጋዜጣ
“ምንሊክ በሰላም ጊዜ የቤት ክርስቲያን አባል በጦር ጊዜ ደገሞ፥ ተዋጊ ንጉሥ ነው ሰለዘመናዊው አለም ዜናም አእምሮው ክፍት ነው:: ” ማርገሪ ፐርሐም::
ምንሊክ የጋዜጣን ታሪክ ቢያውቁም ኣለጋዜጣ ሰራተኛነት ሰው በማጣት ቆዩቶ ገብረ እግዚያበሕር የተባሉ የሐማሴን ተወላጅ በ1888 ዓ ም በሰኔ ወር ከኢጣሊያኖች ሕረር ልዑል ራስ መኮንን ዘንድ ገቡ ሰለኣኢትዮጵያ ባላቸው ፊቅር ምክንያት በዙ የስልጣን ነገሮችን አንደሚናገሩ ምንሊክ ሰሙ ምንሊክ በኣቶ ገብረ ኣአግዚያብሒር ንግ ግራ አየተደሰቱ መኮንን ባይቀየመኝ ይኽን ሰውየ ለኔ አደርገው ነበር አያሉ ለየምኳንንቱ ይናገራሉ ።
በዚህ መሐል ልዑል ራስ መኮንን ሞቱ። የአቶ ገብረእግ ዚኣብሔር ደጋፊ ራስ መኮንን ሲሞቱ የሐረርጌ መኴንንት ኣቶ ገብረ እግዚያብሔርን ከሰሰ ። የከሰሱዋቸውም ይሰድብዋቸው በነበረው ስድብ ሳይሆነ መሬት ትዞራለች እንጂ ፀሐይ አትዞርም ብለህ ተናግረሃል ብለው ነው።
አፄ ምንሊክ ይህንን አንደሰሙ የሐረርጌ ግዛት ለተሰጣቸው ለራስ መኮንን ልጅ ለደጃች ይልማ ደብዳቤ ጽፈው ገብረ አግዚያብ ሔርን ወደ ኣዲስ ኣአበባ ኣአስመጧቸው። ከዚህ በዃላ ሐረር ሆነው የናገሩት የነበረውን ሁሉ በወረቀት እየፃፉ ለየመኳንንቱ እንዲያድሉ አዘዟቸው። ይህም ልክ እን ደጋዜጣ በእጅ አየተፃፈ በየሣምንቱ በምንሊክ ግብር ላይ ይታደል ጀመር። በሥራው የተደሰቱት ምኒልክ በብዛቱ ማነስ ይበሳጩ ጀመር።
ግሪካዊው ካባዲአስ ደገሞ ለሚኒሊክ ባቀረቡት ምክር የጋዜጣ መልክ ያለው በእጅ እየተፃፈ በየሣምንቱ 24 ግልባጭ እየወጣ ለመኳንንቱ ይታደል ጀመር። የዚህንም ስም ምኒልክ ራሳቸው አእምሮ ብለው ሰየሙት። ኮፒ ማድረጊያ መሣርያ በመገኘቱም በየሣመንቱ የአእምሮ 200 ኮፒ ሆነ። ይህን የተመለከቱት ምኒሊክ በካባዲአስ ሥራ ተደስተው ኣዘጋጁ በሥራው እንዲገፋበትና የማተሚያመኪናዎች እንደሚያሰመጡላቸው ተስፋ ሰጧቸው። የእጅ ፁፉን ማብዛቱ ሥራ ግን በ 1895 ዓ .ም ቆመ። የማተሚያው መኪና እስክ1898 ዓም ድረስ አልመጣም ነበር።
ማተሚያ መኪና በኢድልቢ ኣስመጭነት ከመጣ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በሕትመት ጎህ የተባለ ጋዜጣ ወጣ። ይህ ጎህ ተብሎ የተሰየመው ጋዜጣ 1900 ዓም ሐምሌ 17 ሞቀን ታተሞ ሲወጣ የያዘው ፅሑፍ የሚከተለው ነበር።
እጅግ የተወደዳ ችሁ ኢትዮጵያውያን ሆይ ሰሚ ጆሮ ልባዊ አአምሮ ይስጣችሁ ብዬ ሰላምታ አቀርባለሁ።
ከበዙ ዓመት ከብዙም ዘመን በኋላ አኔ የኢትዮጵያ ጎህ የምሆነው ዜናዊ ግዜጣ በግርማዊ ገናና የኢትዮጵያ ነጉሠ ነገሥት ትእዛዝ ነጋድራስ ኃይለ ጊዮርጊስ ከኢትዮጵያ መንገሥት የውጭ ምንስትርነት የተሾምመ። በሙሴ ኤድልቢ እጅ ከኤሮጳ ወደ አዲስ አበባ አስምጡኝ።
የኢትዮጵያ ሕዝብም የሰው ልብ ቶሎ የሚከፍት፥ ከስንፍናም የምታነቃ ብርሃን መጣህልን ብልው ትንሹ ትልቁ በክብር ተቀበሉኝ።ለእግዚያብሔር፤ለመንግስት የሚጠቅም ሥራም ላትምላች ሁ ተሰናዳሁ። ስለዚህ ይህን ሥራ አይቶ ቃሌንም ሰምቶ የማይነቃ ሰው ዬኤሊን ስንፍናዋን የጉጉት በቀን አላማየትዋን ይመስላል። ነገር ግን የነጋድራስ ኃይለጎርጊስ የውጭ ምንስተር ፥ጃንሆየና ንገስታቸን ፥መንግስታችንም ወደውሃል ሁሉም ይሰሙሃል ፥ስምህንም ጎህ ብለው ሰይመውልሃልና ደስ ይበልህ ስላሉኝ በዚህ ቀንም ሰው ሁሉ ሕያው ሁን ጎህ ኣጋዣችን ሆይ ብለው መረቁኝ በታላቅ ደስታ በክበር ዋልኩ። የክርስቲያን ኣባቶቼም ፥ራሶች፥ ሊቃውንቶች ፥ምንስትሮች ፥ደጅ ኣዝማች ፥ወምበሮች ፥ፀሀፊዎች፥ መኳንንቶች ሁሉ ናችው። አምላከ ኢትዮጵያ ይክበር ይመስገን በአይሮጳ ፥በእስያ ፥በኣሜሪካ ፥ባአፍሪቃ ፥በአውስትራሊያም ከእንቅልፋቸው አንቅቼ በእውቀት አስከ አየር አንዳደረስኳቸው ዛሬም ወደ አትዮጵያ እጆችዋን ወደ አግዚአብሔር ከምትዘረጋ አገር ያመጣህኝ።
እድሜ ለምንሊክ ከነሰራዊቱ በዬ እፀልያለሁ።
የኢትዮጵያ አውነተኛ አገልጋይ። ጎህ ሐምሌ 17ቀን 1900ዓመተ ምህረት ዓዲስ ኣበባ
እግቢ ታተመ